Fana: At a Speed of Life!

በትብብር ከሠራን የማናሳካው ሪፎርም፤ የማይደረስበት ብልጽግና አይኖርም” -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትብብር ከሠራን የማናሳካው ሪፎርም፤ የማይደረስበት ብልጽግና አይኖርም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷”አብዮት በጎውን ከክፉው አጃምሎ ጠርጎብናል፤ተሻጋሪ ተቋሞች ለመገንባት አላስቻለንም ነው ያሉት።

ለዚህ ነው ሪፎርምን የመረጥነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን ብለዋል።

በዚህ ዕሳቤ ታላላቅ ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፤ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ ዘርፍ፣ የሕግ፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን እያሳካን በመጓዝ ላይ ነን ሲሉም ገልጸዋል።

በትብብር ከሠራን የማናሳካው ሪፎርም፤ የማይደረስበት ብልጽግና አይኖርም” በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.