Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ለመቄዶንያ የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እና የባንኩ የሥራ አመራር አባላት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረገው ድጋፍ ማዕከሉ በአዲስ አበባ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋውያን ማረፊያና ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ የሚውል መሆኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከሉ በለጋሾች ድጋፍ ብቻ የበርካቶች ሕይወት እንዲስተካከል፣ ከሕመም እንዲፈወሱና ከጉዳት እንዲያገግሙ እያደረገ ያለና አዲስ አበባን ጨምሮ በ33 የክልል ከተሞች ማዕከል በመክፈት ለበርካታ ዜጎች እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.