Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

“የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች” በሚል መሪ ሐሳብ በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው በዓሉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ሀላፊ ሁሴን ሀሺን (ዶ/ር) ጨምሮ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሁሴን ሀሺ (ዶ/ር) በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከለውጡ ወዲህ በክልሉ ጠንክሮ ከተሰራ ወደተሻለ ስኬት ለመሻገር የሚያስችል ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በክልሉ በግብርና፣ ቱሪዝም፣ በማዕድንና ነዳጅ፣ በውሃ እና አረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በየዘርፉ ያለውን ዉጤታማ ስራ በማስቀጠል በቀጣይ ትኩረት ባልተሰጣቸው የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፎች ላይ በስፋት በመስራት የተፈለገውን ብልፅግና ይዘን መሻገር ይኖርብናል ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.