Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፓኪስታን በታክስ አስተዳደር ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በፓኪስታን ንግድና ኢንቨሰትመንት ሚኒስትር ባሲት ሳሌም ሻህ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ወ/ሮ ዓይናለም÷ ፓኪስታን የኢትዮጵያን የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ማዘመን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት መወሰኗ የተጀመሩት የታክስ ማሻሻያ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የራሱ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

የፓኪስታን ልዑካን በበኩላቸው÷በሀገራቸው ተግባር ላይ የዋሉና ውጤት ያመጡ እንደ ኤሌክትሮኒክ ኦዲትና የታክስ ዲጂታይዜሽን ያሉ ተሞክሮዎችን ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ የሁለቱ ሀገራት ትብብር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይ በሀገራቱ ያሉ የታክስ አስተዳደር ልምዶችን ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት መስማማታቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.