Fana: At a Speed of Life!

ምስራቅ ዕዝ በመላ የሀገሪቱ በመሰማራት የሀገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ ጀግና ዕዝ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት አንዱ አካል የሆነው ምስራቅ ዕዝ በምስራቁ የሀገራችን ቀጠና ብቻ ሳይወሰን በመላ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመሰማራት የሀገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ ጀግና ዕዝ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፤ ለምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አመራሮች፣ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የሀገሩን ዳር ድንበር ሰያስከብር የኖረው ምስራቅ ዕዝ ልክ እንደ ወትሮ ሁሉ ታሪኩን ማስቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በቀጣይም ሀገራችሁን ከጠላት እንደምትከላከሉ እምነታችን ነው፤ ተቋሙ በእናንተ ይኮራል ሲሉም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.