Fana: At a Speed of Life!

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ 900ኛ ግቡን አስቆጠረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በትናንትናው እለት ሀገሩ በኔሽንስ ሊግ ክሮሺያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ባስቆጠራት ግብ አማካኝነት አዲስ ታሪክ ጽፏል።

በዚህም በጨዋታ ዘመኑ ያስቆጠረውን የግብ መጠን 900 በማድረስ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል፡፡

በፈረንጆቹ 2004 በአውሮፓ ዋንጫ ለሀገሩ መጫወት የጀመረው ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 131 ግቦችን በማስቆጠር የሚስተካከለው የለም፡፡

በዚህ ዓመት በሻምፒዮናው ከተሳተፉ 368 ተጫዋቾች መካከል በአሁኑ ወቅት እግር ኳስን እየተጫወተ የሚገኘው ንም ዕየተጫወተ የሚገኘው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በክለብ እግር ኳስ ህይወቱ አሁን እየተጫወተ የሚገኝበትን የሳውዲው አልናስርን ጨምሮ ለስፖርቲንግ ሊዝበን፣ ማንቼስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ ባጠቃላይ 769 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

ተጫዋቹ 437 ግቦቹን ያስቆጠረው እድሜው 30 ከገባ በኋላ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል።

900 ግቦችን በማስቆጠር የምንጊዜም ከፍተኛ የግብ አግቢነት ክብረ ወሰንን በእጁ ያደረገው ሮናልዶ፤ 1 ሺህ ግቦችን የማስቆጠር ህልም ሰንቋል።

በሳዑዲው ክለብ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ሮናልዶ በሚያስቆጥራቸው ግቦች ክለቡን ባለድል እያደረገ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.