Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ የኢንቨስትመንት ሃብቷን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ የቢዝነስ ፎረም ላይ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ሃብት አስተዋውቃለች፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣በቱሪዝም፣ በአይሲቲ፣ በማዕድን ኢነርጂና ሌሎች ዘርፎች እምቅ ሃብትእንዳላት ለፎረሙ ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እና አማራጮች ያላት ሀገር መሆኗን ገለጻ አድርገዋል፡፡

በፎረሙ ከ600 በላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ የቻይና ባለሃብቶችና ኩባንያዎች መሳተፋቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.