Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና በ17 ዘርፎች በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዛሬ ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

ቀደም ብሎ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ላይ ከእኛ የዕድገት እና የልማት ግቦች ጋር የሚናበቡ 10 ነጥቦች ያሉት የድርጊት መርሐ ግብር ይፋ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም ያደገ ምርታማነትን ለማሳካት ሥራዎቻችንን በምናዘምንበት የግብርና ትብብር መንገድ ላይ ፍላጎታችንን ገልጫለሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በኢንዱስትሪ ልማት እና በዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ላይ ድጋፍ በሚገኝበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ በጋራ በተገኙበት ኢትዮጵያና ቻይና በ17 ዘርፎች በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውንም ተናግረዋል፡፡

ስምምነቶቹ በኢትዮጵያ እና በቻይና ላለው በሁሉም ሁኔታ ለማይለዋወጠው ስትራቴጂያዊ ትብብር ዓይነተኛ ማሳያ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.