Fana: At a Speed of Life!

 ውሃና ኢነርጂ ጉዳይ ከዜጎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው በመሆኑ በፋና ልዩ ሽፋን ይሰጠዋል – አቶ አድማሱ ዳምጠው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ጉዳይ ከዜጎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው በመሆኑ ልዩ ሽፋን ይሰጠዋል ሲሉ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ተናገሩ፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራሮች ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ፋና በመዝናኛ ፣ በትምህርታዊ ፕሮግራሞችና በዜና ዘገባዎች ሰፊ ተደራሽነት ያለው ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋም ነው፡፡

ፋና ሕብረተሰቡን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸው÷የውሃና ኢነርጂ ጉዳይም ከዜጎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በበኩላቸው÷ ስለ ውሃና ኢነርጂ ሃብት መረጃ በመስጠት፣ በማስተማርና በማሳወቅ ሒደት ውስጥ ሚዲያ ትልቅ ሚና መጫወት እንደሚገባው አንስተዋል፡፡

በተለይ የውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች ሰፊ የማሳወቅና የማስተማር ሥራ የሚጠይቁ በመሆናቸው ከሚዲያ ጋር ሰፊ ሥራዎች መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.