Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ በቁጭት ወደ ስራ መግባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዜጎችን ጤና መጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው በሚል እልህና ቁጭት በሙሉ አቅም ወደ ስራ መግባት እንደሚያስፈልግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የጤና ልማትና ኢንቨስትመን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዓመታዊ ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ÷ አመራሩ የሚመራበትን ስርዓት በየጊዜው መገምገምና ጉደለቶችን በመለየት ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ሕክምናንን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት፣ በህክምና ተቋማት ተከማችተው የሚገኙ ግብዓቶችን በአግባቡ በመጠቀምና ለህብረሰቡ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

የዜጎችን ጤና መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን በመግለጽ፤ በእልህና ቁጭት በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለመግባት መነሳሳት እንደሚያስፈልግም መግለጻቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ዞኖች እውቅና እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.