Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የቡና ምርታማነትን ለማሳደግና የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳለጥ ያለመ ንቅናቄ በሃዋሳ እየተካሄደ ነው፡፡

በንቅናቄ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ÷ የሲዳማ ቡና በሀገሪቱ የውጪ ምንዛሪን በማስገኘት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል፡፡

ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በዓለም አቀፍ ውድድር የሲዳማ ቡና በአንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

አሁንም ላይ ክልሉ የቡና ምርት ላይ መስጠት ከሚገባው በታች እያመረተ መሆኑን ጠቁመው÷ቡና አብቃይ አካባቢዎች እድሉን በአግባቡ በመጠቀም ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ቡና እንዲያመርቱ አሳስበዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው÷ የቡና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለመጨመር በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.