Fana: At a Speed of Life!

በፓሪስ ኦሊምፒክ የተሳተፈችው አትሌት ፍቅረኛዋ ባደረሰባት ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዑጋንዳዊቷ የማራቶን ሯጭ ርብቃ ቼፕቴጌ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፍቅረኛዋ በደረሰባት ጥቃት አብዛኛው የሰውነቷ ክፍል በእሳት ከተቃጠለ ከቀናት በኋል ለህልፈት ተዳርጋለች፡፡

በአትሌቷ እና ፍቅረኛዋ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ቤንዚን በላይዋ ላይ በማርከፍከፍ በእሳት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት መገለፁ ይታወቃል፡፡

በክስተቱ ፍቅረኛዋም መጎዳቱና ሁለቱም ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር፡፡

ነገር ግን አትሌቷ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ሕይወቷ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.