288 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 288 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከነሐሴ 17 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የያዘው፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የግንባታ ግብዓቶች፣ ወርቅ፣ የምግብ ዘይት፣የጦር መሳሪያና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ ጅግጅጋ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።