Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ከታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነጥብ ተጋርቷል፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ላይ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም የተደረገው ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቅቋል፡፡

ዋልያዎቹ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም በታንዛኒያ እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.