በጋምቤላ ክልል 13ኛው የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል “በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሃሳብ 13ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው በ2016 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንደሚገመግምና ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በ2017 የትምህርት ዘመን በሚተገበሩ ስራዎች ዙሪያ ጉባኤው ተወያይቶ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።
በክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።