Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሚያደርጋት ሁኔታ በፍጥነት እያደገች ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሚያደርጋት ሁኔታ በፍጥነት እያደገች ነው ሲሉ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን-አፍሪካን አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች÷ ከመላው አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ለተውጣጡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ብቻ ሳትሆን የፓን አፍሪካን ንቅናቄ የተወለደባት የአፍሪካ ነፃነት ቀንዲል ናት ያሉት ከንቲባዋ÷ ዛሬ የተሰባሰብንበት የዚሁ ውጤት ማስታወሻ እንዲሆን በተሰየመ አዳራሽ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቅርብ መሪነትና በመላው የከተመዋ አመራር የተቀናጀ ርብርብ ውጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በአመራር ዘመናችን የመንግሥት እና የህዝብ አቅሞችን በማስተባበር ከተማን መለወጥና አቅሞችን አስተባብሮ ማልማት እንደሚቻል አረጋግጠናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ባለፉት ዓመታት ሰው ተኮር አቅጣጫን በመከተል የዜጎችን ሕይወት በተጨባጭ የሚለውጡ ሥራዎች ማከናወን ችለናል ነው ያሉት፡፡

ከመደበኛ ሥራዎች በተጨማሪ በቅርቡ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አስደማሚ ውጤት እያመጡ እንደሚገኙ ማንሳታቸውንም የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.