ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሀሳብ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በፎረሙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከ47 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን ፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በፎረሙ የኢትዮጵያ ከተሞች ተሞክሯቸውን ለአቻ የአፍሪካ ከተሞች በማጋራት የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል ተብሏል።
የፎረሙ ታዳሚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡