Fana: At a Speed of Life!

በወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሰለጠኑ የፖሊስ አመራርና አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በአዋሽ ቢሾላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በወንጀል ምርመራ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ አመራርና አባላትን አስመርቋል፡፡

የኮሌጁ ዋና ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር ጎሳዬ ከበደ በዚህ ወቅት÷ ስልጠናው የፖሊስ አመራርና አባላት ሙያዊ እውቀትና ክህሎት የሚያሳድግ እና በሥራ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት ለሕብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የህዝብ እና የመንግስት ጥቅም የሚረጋገጥበት፣ በህዝብ ዘንድ ፍትህን በማስፈን የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበትና የተጎጂዎች እንባ የሚታበስበት ነው ሲሉም መናገራቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመራቂዎቹ በቀጣይ ሕብረተሰቡ የሚገባውን ፍትህ የበለጠ እንዲያገኝ በታማኝነት እና በቅንነት እንዲያገለግሉ ምክትል ኮሚሽነር ጎሳዬ ከበደ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.