Fana: At a Speed of Life!

ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በአንደኛነት ያጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአፍሪካ በአንደኛነት ያጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

 

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ6 ወርቅ 2 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በውድድሩ ተሳታፊ ለነበሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ በነገው እለት የዕውቅና እና የሽልማት መርሐግብር የሚደረግ ይሆናል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.