የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሀሳብ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016ዓ.ም በሚካሄደው ፎረም ÷ ከ47 በላይ የአፍሪካ ሀገራት፣ ከ30 በላይ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ1ሺ 500 በላይ ታዳሚዎች እንደሚታደሙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፎረሙ የኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል በሆነው የዓድዋ ሙዚየም እንደሚከናወንና ኢትዮጵያ አንደ ሀገር ዲፕሎማሲያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሞችን እንደምታገኝበት ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተሞክሯቸውን በማጋራት ከአቻ የአፍሪካ ከተሞች ልምድ እንደሚቀስሙ የሚጠበቅ ሲሆን÷አጋጣሚውን በመጠቀም ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት ዕድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች እንግዶቹን በተለመደው ጨዋነት እንዲቀበልም ጥሪ ቀርቧል፡፡