በፓሪስ ኦሊምፒክ የተሳተፈችው አትሌት ፍቅረኛዋ ባደረሰባት ጥቃት በእሳት መቃጠሏ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዑጋንዳዊቷ የማራቶን ሯጭ ርብቃ ቼፕቴጌ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፍቅረኛዋ በደረሰባት ጥቃት አብዛኛው የሰውነቷ ክፍል በእሳት መቃጠሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በአትሌቷ እና ፍቅረኛዋ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ቤንዚን በላይዋ ላይ በማርከፍከፍ በእሳት አቃጥሏታል ያለው የትረንስ ኖዚያ ፖሊስ÷ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ገልጿል፡፡
በክስተቱ ፍቅረኛዋም መጎዳቱ የተገለጸ ሲሆን÷ ሁለቱም ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን አይሪስ ኤግዛማይነር ዘግቧል፡፡
አትሌቷ በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ የሴቶች ማራቶን ተሳትፋ 44ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቋቋ ይታወሳል፡፡