Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ 3 ሜዳሊያዎች በማግኘት ተሳትፎዋን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው 17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያ 2 የወርቅና 1 የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ተሳትፎዋን አጠናቅቃለች።

በዚሁ መሠረት አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የጭላንጭል (T-13) እና ያየሽ ጌቴ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የአይነ ስውር (T-11) የወርቅ ሚያዲያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ይታያል ስለሺ በ1 ሺህ 500 ወንዶች አይነስውር ጭላንጭል (T-11) የብር ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በ17ኛው የፓራሊምፒክ ተሳትፎዋ በ2 የወርቅ እና 1 ብር ሜዳሊያዎች ከዓለም 28ኛ ደረጃ ላይ ሆና ውድድሩን ማጠናቀቋን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዘንድሮው ውጤትም ከ16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች አንጻር የተሻለ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.