Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የሁቲ አማጺያን የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ማዕከልን አወደመች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀይ ባህር ላይ የነበሩ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ አሜሪካ የሁቲ አማጺያን ሚሳኤል የሚያስወነጭፉባቸውን ማዕከል አወድማለች፡፡

የአሜሪካ ጦር በየመን በሁቲ አማጺዎች ቁጥጥር ስር ባለዉ አካባቢ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቡድኑ በቀይ ባህር ላይ በሁለቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ትናንት ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ነው ማዕከሉ መውደሙን ያስታወቀው።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ፥ ለአሜሪካና ለሌሎች ጥምር ኃይሎች እንዲሁም የንግድ መርከቦች ስጋት የሆነውን ሁለቱ የሚሳኤል ማዕከሎች አውድሜያለሁ ብሏል፡፡

አክሎም፥ እርምጃው የተወሰደው ዓለም አቀፉን ውሃን ለአሜሪካና ለጥምር ሃይሎች እንዲሁም ለንግድ መርከቦች ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ነው ብሏል፡፡

የአሜሪካ ጦር ሃይሎች ሰኞ ዕለት በቀይ ባህር ላይ በነበሩ ሁለት የነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የሀገሪቱ ጦር ሃይል ገልጾ እንደነበር ይታወቃል።

የሁቲ ታጣቂ ኃይሎች በሁለት ባላስቲክ ሚሳኤሎች እና በአንድ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመታገዝ በመርከቦቹ ላይ ጉዳት መድረሳቸውን ዕዙ አስታውሷል።

የሁቲ ቡድን ከእስራኤል ሀማስ ጦርነት ጋር በተገናኘ እስራኤልን በመቃወም ጥቃት መፈጸሙን ካሳወቀ በኋላ አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 ታህሳስ ወር የብዙ ዓለም አቀፍ ጥምረት መመስረቷ ይታወሳል።

የቡድኑ ተግባር ከጊዜ በኋላ ከአሜሪካ እና ከብሪታኒያ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መርከቦችን ኢላማ ማድረጉንም ነው ዘ ፔኒንሱላ የዘገበው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.