Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 31 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በሰው እገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 31 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ እንዳሉት÷በከተማዋ የእገታ የወንጀል ድርጊቶች ተፈጽመዋል።

የጸጥታ መዋቅሩ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ባደረገው ክትትል 31 የእገታ ወንጀል ፈጻሚ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ተናግረዋል።

ፖሊስ በወንጀል ፈጻሚ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ምርመራ በማካሄድ 16 የክስ መዝገቦችን አጣርቶ ለፍትሕ አካላት ማቅረቡን አስረድተዋል።

በተጨማሪም 17 የክስ መዝገቦችን ደግሞ እየመረመረ መሆኑን ጠቁመው÷ በቅርቡ አጠናቅቆ ወደ ፍትህ አካላት ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በፍርድ ቤት የፍለጋ ትዕዛዝ የተላለፈባቸው ከ10 በላይ እገታ ፈጻሚ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፖሊስ ጥብቅ ክትትል እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

በከተማው የጸጥታ ስራ ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡ የስነ ምግባር ጉድለት የፈጸሙና በወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ 14 የጸጥታ አባላትም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን አብራርተዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.