Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ መርሐ-ግብር የሚተገበሩ ፕሮግራሞችን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የሚተገበሩ ፕሮግራሞችን ይፋ አድርጋለች፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ÷ ከነገ በስቲያ በሚጀመረው የቻይና-አፍሪካ ጉባዔ ላይ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ ቤቶች ልማት፣ ፈጠራና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን ጨምሮ የቤልት ኤንድ ሮድ ሥራዎች ይቀርባሉ ብሏል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም እንዲፈቱ ቻይና አጋርነቷን እንደምትቀጥልም መግለጫ አረጋግጧል፡፡

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በመሰረተ-ልማት እና በኢኮኖሚ ትብብር ስትሠራ መቆየቷን ያወሳው መግለጫው÷ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድን በማሳያነት ጠቅሷል፡፡

ቻይና የቤልት ኤንድ ሮድ መርሐ-ግብርን በ52 የአፍሪካ ሀገራት ለመተግበር ስምምነት መፈራረሟም ተመላክቷል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.