የባሕርዳር ስታዲየም ግንባታ የፊፋ ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ እየተከናወነ ነው – ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡
ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የባህርዳር ስታዲየም ደረጃውን ጠብቆ እንዲሰራ የክልሉ አመራሮች የወሰዱት ቁርጠኝነት ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ነው።
ስታዲየሙ የስፖርት ቱሪዝም እና የክልሉ ምጣኔ ሃብት እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል፡፡
የባሕርዳር ስታዲየም የፊፋ ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የተጀመሩ ስታዲየሞች ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁና ለተሰሩበት ዓላማ እንዲወሉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መጠየቃቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡