Fana: At a Speed of Life!

ሞሐመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ በ2024/2025 የውድድር ዓመት መጨረሻ ከክለቡ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

ትናንት ሊቨርፑል በታሪካዊ ተቀናቃኙ ማንቼስተር ዩናይትድ ላይ ከተጎናጸፈው ድል በኋላ ለስካይ ስፖርት በሰጠው አስተያየት÷ “በዚህ ዓመት መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ልለያይ እችላለሁ፤ የኮንትራት እናራዝምልህ ጥያቄ ያቀረበልኝ አካልም የለም” ብሏል፡፡

በፈረንጆቹ 2022 የሦስት ዓመት ኮንትራቱን ያራዘመው ሞሐመድ ሳላህ÷ በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ ነው በተባለለት 350 ሺህ ፓውንድ ሣምታዊ ክፍያ በቡድኑ ስኬታማ ሕይወት እያሳለፈ ይገኛል፡፡

በክረምቱ የዝውውር መስኮት የሳዑዲው አል-ኢቲሃድ ሞሐመድ ሳላህን ለማዘዋወር 150 ሚሊየን ፓውንድ ቢያቀርብም በሊቨርፑል ውድቅ መደረጉን አስታውሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የ32 ዓመቱ ግብፃዊ የእግር ኳስ ኮከብ በሊቨርፑል ቆይታው የፕሪሜር ሊግ ዋንጫን ጨምሮ የአውሮፓ ሻምፕዮንስ ሊግን እና በርካታ ክብሮችን መጎናፀፍ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.