1 ሺህ 254 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 254 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ተመላሾቹ 945 ወንዶች፣ 262 ሴቶችና 47 ጨቅላ ሕፃናት ሲሆኑ ፥ ከእነዚህ መካከልም 103 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።