አርሰናል ስተርሊንግን፤ ቼልሲ ደግሞ ሳንቾን አስፈረሙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ማጠቃለያ ላይ አርሰናል ራሂም ስተርሊንግን፤ ቼልሲ ደግሞ ጃዶን ሳንቾን አስፈርመዋል።
አርሰናል የቸልሲውን ራሂም ስተርሊን በአንድ ዓመት የውሰት ውል ማስፈረሙ ተገልጿል።
እንዲሁም በክረምቱ የዝውውር መስኮት የነቃ እንቅስቃሴ የነበረው ቼልሲ የማንቼስተር ዩናይትዱን የክንፍ ተጫዋች ጃዶን ሳንቾን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡