Fana: At a Speed of Life!

ፓርኩ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ መተካት ላይ በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የወጪ ንግድን ለማሳደግ እና ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጋራ ለሦስት ቀናት የሚዲያ ቱር አካሂደዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት÷ ፓርኩ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን መተካት፣ ኤክስፖርትን ማሳደግ፣ ቴክኖሎጂን ማሸጋገር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሌሎች ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ላይ በትጋት እየሠራ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣውን ቆሻሻ እያከመ መልሶ ሥራ ላይ እንዲውል በማድረግ የአካባቢ ብክለት ሥጋት አስቀርቷል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.