Fana: At a Speed of Life!

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለነጻ አህጉራዊ የንግድ ትስስር ፋይዳው የጎላ ነው – ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢንቨስትመንትና ንግድን በማሳለጥ ሀገሪቱን በነጻ አህጉራዊ የንግድ ትስስር ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የአፍሪካ ነጻ አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የአፍሪካ ነጻ አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ከሆኑት ዋምኬሌ ሜኔ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፥ ለስምምነቱ የተሟላ አፈፃፀም ለተቋማትና ለግሉ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት ወሳኝ መሆኑን አምባሳደር ታዬ በአፅንኦት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች ኢንቨስትመንትና ንግድን በማሳለጥ ሀገሪቱ በነጻ አህጉራዊ የንግድ ትስስር ተጠቃሚ እንድትሆን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.