ብሪክስ በአፍሪካ ሀገሮች መነቃቃት እንዲፈጠር ማድረጉ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ ለአፍሪካ ሀገራት መነቃቃት የፈጠረና ከተለያዩ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በር የከፈተ ስለመሆኑ በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የብሪክስ ተወካይ አምባሳደር ሳምሶንደን ኦላጉንጁ ተናገሩ።
ብሪክስን በመወከል በተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚያስፈጽሙ ተወካይ አምባሳደሮች (ኢንተርናሽናል ሙኒሲፓል ብሪክስ) ጉባዔ በሩሲያ ሞስኮ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ተወካይ አምባሳደር ሳምሶንደን ኦላጉንጁ እንደተናገሩት፤ የብሪክስ ጠንክሮ መውጣት የአፍሪካ አህጉር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አማራጭ እንዲኖረው አስችሏል።
የአማራጩ መስፋት በአፍሪካ ሀገሮች ዘንድ ኢኮኖሚውን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መነቃቃት ፈጥሯል ብለዋል።
የብሪክስ ድጋፍን በመጠቀም አህጉራዊ ኢኮኖሚውን ከጫና ለማላቀቅ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የብሪክስ ሀገራት ተሞክሯቸውን በማካፈል ረገድ የተለያየ ስራ እያከናወኑ መሆኑ መገለጹን አርቲ ዘግቧል።