Fana: At a Speed of Life!

የአቪዬሽን መመሪያና ደንቦችን ተቀብሎ መተግበር ይገባል – ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቪዬሽን መመሪያና ደንቦችን ተቀብሎ መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የአየር ትራንስፖርት ተሳፋሪ መንገደኞች ሊተገብሯቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር ግዴታዎችን አስመልክቶ ግንዛቤ ለመስጠት ያለመ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናው ናቸው አበይት ተግባራት ውስጥ አንዱ የበረራ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ዘርፈ ብዙ የበረራ ቁጥጥር ስራዎች አንዱና ዋንኛው ነው ተብሏል፡፡

እነዚህ የቁጥጥር ስራዎች ዓለም አቀፍ አሰራርን መሰረት ያደረጉና የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶችና ደረጃዎችን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ ናቸው፡፡

እነዚህ መስፈርቶችና ደረጃዎች አየር መንገዶች በጥንቃቄ ሊተገብሯቸው የሚገቡ አሰራሮችን የሚያመለክት ሲሆን ፥ የቁጥጥር ስርዓቱ ዋነኛ ዓላማም የበረራ ደህንነትን በማረጋገጥ የተሳለጠ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የበረራ ደህንነትን ማረጋገጥ የአየር መንገዶች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመንገደኞች ሃላፊነትም ጭምር እንደሆነ ያስታወቀው ባለስልጣኑ ፥ የመግለጫውም ትኩረት መንገደኞች የተጣለባቸው ኃላፊነቶችና ማግኘት የሚገባቸውን መብቶች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታለመ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም ባለስልጣኑ እነዚህን ዓለም አቀፍ ህጎችና አሰራሮች ሳይሸራረፉ መተግበራቸውን ዕለት ተዕለት የሚከታተልና የሚቆጣጠር ተቋም እንደመሆኑ ከተሳፋሪዎች የሚጠበቁ ህጋዊ ግዴታዎችና ኃላፊነቶችን እንዲያውቁት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ተሳፋሪዎች ሊከተሉት ከሚገባ ህጎችና ደንቦች ውስጥ የአየር መንገዶች ሰራተኞችና የሚያስተላልፉትን መመሪያና ደንቦች ተቀብሎ መተግበር ዋነኛው እንደሆነም መገለጹን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም በዋናነት በአውሮፕላኖች ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጨዋነት የጎደለውና የሚረብሽ ባህሪ መልካም ስርዓትን እና ዲሲፕሊንን የሚጎዳ ከመሆኑም ባሻገር የአውሮፕላኑን እና የአውሮፕላኑን ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል በመሆኑም ጭምር ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.