የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያት ዋና ጸሐፊ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያት ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ለዋና ጸሃፊው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሐብረቢ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ዋምኬሌ ሜኔ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ያለበት ደረጃና የኢትዮጵያ ተሳትፎ ላይ ምክክር እንደሚያደርጉም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡