ኢራን ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር ዙሪያ ለመደራደር በሯን ከፈተች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
የኢራን ከፍተኛ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ከአሜሪካ ጋር እንደገና ለመደራደር ለሀገሪቱ መንግስት “ምንም እንቅፋት የለም” ብለዋል።
በለውጥ አራማጁ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን መንግስት ለሚደረጉ ማናቸውም ንግግሮች ግልፅ ቀይ መስመር ማስቀመጣቸው የተነገረ ሲሆን፥ አሜሪካ አትታመንም ሲሉ ማስጠንቀቃቸውም ነው የተነሳው፡፡
ካሜኒ በበኩላቸው፥ “ተስፋን በጠላት ላይ ማኖር የለብንም፤ የጠላት ስምምነት እቅዳችንን እንዲቀጥል መጠበቅ የለብንም” ብለዋል።
የ80 ዓመቱ አያቶላህ አሊ ካሜኔ የፔዜሽኪያንን ካቢኔ “አትመኗቸው” ሲሉም አስጠንቅቀዋል ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡
አያቶላህ በአብዛኛው በሁሉም የኢራን መንግስት ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሲወስኑ ይታያሉ፡፡