Fana: At a Speed of Life!

ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገቢሳ ኤጀታን (ፕ/ር) በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ምሁር ሲሆኑ÷ በዚህ ለወገን ጠቃሚ ተግባራቸውም በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተችሯቸዋል፡፡

በተለያየ ጊዜ 17 ከፍተኛ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት ፕሮፌሰሩ÷ በቅርቡ “ኦርደር ኦፍ ግሪፊን እና ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ተሸልመዋል፡፡

አሁን ደግሞ በፑርዱ ዩኒቨርሲቲ የዓመቱ ምርጥ ሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመርጠዋል፡፡

ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ ከ70 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማማከር ከ200 በላይ የምርምር ውጤቶችን ለኅትመት አብቅተዋል፡፡

የሮክፌለር ፋውንዴሽን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዲሁም የአሊያንስ ግሪን ሪቮሉሽን የክብር አባል ለመሆንም በቅተዋል፡፡

ከሮክፌለር፣ ከሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በትብብር የሚሠሩት ተመራማሪው፥ የሣይንስ ካውንስል፣ የሣሣካዎ ግሎባል የቦርድ አባልም ናቸው፡፡

ቀደም ሲልም የ “ወርልድ ፉድ ፕራይዝ” ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ጥገኛ አረምን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ለማዳቀል ለሚሠሩት ምርምርም ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች 5 ሚሊየን ዶላር ያገኙት ምሁሩ÷ በአሳለፍነው ጥቅምት የ “አሜሪካን ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ሽልማትን ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.