Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከፌስቡክ ላይ የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች እንዲነሱ ግፊት አድርጋ ነበር ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሥተዳደር በ2021 የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች ከፌስቡክ እንዲወገዱ ለወራት በተደጋጋሚ ግፊት ማድረጉን የሜታ ኩባንያ መስራች ማርክ ዙከር በርግ አመላከቱ፡፡

ዙከር በርግ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የፍትሕ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ÷ በባይደን አሥተዳደር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት አስቂኝና ቀልድ አዘል መልዕክቶችን ጨምሮ አንዳንድ የኮቪድ-19 ይዘቶችን ሳንሱር ለማድረግ ግፊት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የባይደን አሥተዳደር የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጎጂ የሆኑና የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዲያስወግዱ መጠየቁን ደግፎ እንደነበርም ዘ ኢንዲፐንደንት ዘግቧል፡፡

በተደጋጋሚ የተደረገውን ግፊት ተቋማቸው ለዓለም አለማሳወቁ የቆጫቸው ዙከርበርግ÷ እንዲህ ያለ ተጽዕኖ ድጋሜ ከተፈጠረ እንደማይታገሱ አስጠንቅቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.