Fana: At a Speed of Life!

31ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ 31ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆው ጉባዔው “የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በጉባዔው ላይም በ2016 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በመገምገም እንዲሁም የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማት፣ ባለሙያዎችና ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም በ2017 የትምህርት ዘመን የሚተገበሩ ሥራዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.