Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ለተሻለ የተገልጋይ ዕርካታ” በሚል መሪ ሀሳብ 6ኛው የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ሌዳሞ÷ መንግስት የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ መጀምሩን ገልፀዋል፡፡

የፍትህ መሻሻልና ተደራሽነትን ለማስፈን የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ የተጀመረው የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራ እንዲጠናከር የክልሉ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ÷ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካሉ የሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ የፍትህ ሪፎርም መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ምክር ቤቱ ያለውን የፍትህ ሁኔታ በተመለከተ ጥናት ማስጠናቱን ጠቅሰው÷ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራ በምክር ቤቱ መሪነት እየተሰራ ነው ማለታቸውን የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው÷ ሀገራዊ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሁሉም ክልል ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እውነተኛ ፍትህ ለማረጋገጥ ሁሉም የፍትህ ተቋማት ተቀናጅተው እየሰሩ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.