Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በተከታታይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በተለያዩ ቴአትሮች እና ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡

የዝናቧ እመቤት፣ የገንፎ ተራራ፣ የጨረቃ ቤት፣ ዓይነ ሞራ፣ ንጉሥ ሊር፣ ጥሎሽ፣ ጣውንቶቹ፣ ከራስ በላይ ራስ፣ የሸክላ ጌጥ፣ የጫጉላ ሽርሽርና ቅርጫው አርቲስት ኩራባቸው ከተሳተፈባቸው የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከተዋናይነት ባለፈም ቴአትሮችን በመጻፍ በማዘጋጀት ለኪነ ጥበቡ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

አርቲስት ኩራባቸው በ1957 ዓ.ም በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ ሸንኮር ተብሎ በሚጠራው መንደር ነበር የተወለደው፡፡

አርቲስቱ ባለትዳር እና የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጆች አባት እንደነበር ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.