Fana: At a Speed of Life!

የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አረጋ ከበደ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግስት ከህዝቡ የሚነሱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

በቡልጋ ከተማ አስተዳደር በ40 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለህዝብ አገልግሎት በቅቷል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋ በወቅቱ እንደገለጹት÷ በክልሉ ህግ ከማስከበር ጎን ለጎን በሚከናወኑ ተግባራት ህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተቻለ ነው።

በክልሉ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የተጀመሩ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በክልሉ ዘላቂነት ያለው እድገት ለማስመዝገብና የተረጋጋ ስላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ሁሉ ህብረተሰቡ እውቀቱን፣ ሀብቱንና ጉልበቱን በማስተባበር ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዛሬ ለአገልግሎት የበቃው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ60 ቀናት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ መሆኑና ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.