Fana: At a Speed of Life!

“የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያን ይግዙ” የተሰኘ ልዩ የንግድ ሳምንት ዛሬ በይፋ ተከፍቷል፡፡

የንግድ ሳምንቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከፍተዋል።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማኒስቴር በተዘጋጀው የንግድ ሳምንት የተለያዩ አስመጭና ላኪዎች ምርቶችን ለሸማቹ ያቀረቡበት ነው።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተዘጋጀው የንግድ ሳምንቱ ከዛሬ ነሐሴ 19 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማኒስቴር የተገነባውን የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ማሳያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።

ማዕከሉ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸውን የምርት ዓይነቶች የሚያሳይ ነው።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.