Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2 ሺህ 800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2ሺህ 800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል ብለዋል።

በዚህም የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2 ሺህ 800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል በማለት አብስረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል ሲሉም አስገንዝበዋል።

ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን፣ በቀጠናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት በእጅጉ ይጠቅማል በማለት ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.