Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት አሰራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ በልጽጎ ሥራ ላይ የዋለው ሶፍት ዌር አስመልክቶ እንደገለጹት÷ሶፍትዌሩ አቅም ያለውና መጪውን ቴክኖሎጂ መሸከም የሚችል ነው፡፡

የተቋሙ የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ሶፍትዌሩ በተለይ የፍትሕ ሥርዓት ሒደቱን ከማዘመን አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው መጠቆማቸውን የመከላከያ ሰራዊት መህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይ ይግባኝ ሰሚ አካል እየተንቀሳቀሰ የሚሰራውን ሥራ በማቃለል እንዲሁም ወጪና ጊዜን በመቆጠብ ረገድ ሚናው የጎላመሆኑን አስረድተዋል፡፡

እየበለፀጉ ያሉ ሶፍትዌሮች የተቋሙን የአውቶሜሽንና የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት እንደሚያፋጥኑም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.