የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ተሳተፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ተሳትፈዋል።
በዚሁ ወቅትም መሬትን በመንከባከብና በመጠበቅ አርሶ አደሮችም ሆኑ አርብቶ አደሮች ሥራቸውን የተሳካ ለማድረግ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መሬትን ለመንከባከብ እንዲሁም ደኖች እንዲጠበቁ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
#አረንጓዴዓሻራ