Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ማኖር መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ማኖር መርሐ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በዚህ መሰረትም ጎንደር፣ ደሴ፣ ሰቆጣ እና ፍኖተ-ሠላምን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሕብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ እየተሳተፈ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ በአማራ ክልል ባላፉት ዓመታት የተተከሉት ችግኞች ከደን ልማት ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ የአትክልት እና ፍራፍሬዎች መኖራቸው ተመላክቷል።

ችግኞቹ የተፈጥሮ ሚዛንን ለማስጠበቅ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችሉም ተገልጿል።

#600_ሚሊየን_ችግኝ_በአንድ_ጀንበር

#አረንጓዴዓሻራ

#GreenLegacy

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.