Fana: At a Speed of Life!

በግዝፈቱ በዓለም ሁለተኛው ዳይመንድ በቦትስዋና ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትልቅነቱ በዓለም ሁለተኛው እንደሆነ የተነገረለት ዳይመንድ በቦትስዋና መገኘቱ ተሰምቷል፡፡

በዓለም በግዝፈቱ አንደኛው ዳይመድ በፈረንጆቹ 1905 በደቡብ አፍሪካ የተገኘ ሲሆን 3 ሺህ 106 ካራት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አሁን ከቦትስዋና የተገኘው ዳይመንድም 2 ሺህ 492 ካራት መሆኑን እና በግዝፈቱ በዓለም ሁለተኛው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡

የደቡብ አፍሪካዋ ቦትስዋና በዳይመንድ መገኛነት ከዓለም ግንባር ቀደም መሆኗም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.