የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድር የሚሳተፈውን ልዑክ አበረታቱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በፓሪስ በሚካሄደው ፓራሊምፒክ ውድድር የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አበረታቱ፡፡
ወ/ሮ ሸዊት በዚህ ወቅት÷ኢትዮጵያን የወከሉ ስፖርተኞችን አቅም በፈቀደ መጠን በሽኝትም ሆነ በአቀባበል ወቅት ሚኒስቴሩ ከጎናቸው እንደሚሆን ተናግረው በድልና በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት÷በቀጣይ በፓራሊምፒክ ስፖርት ላይ በትኩረት እንደሚሠራ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ አትሌቶችና የቦርድ አመራር አባላት፣ አሰልጣኝና ቴክኒክ ቡድንም÷ ሚኒስቴሩ እያደረገ ላለው ድጋፍ እና ላሳየው አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ ከነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፓሪስ የሚጓዝ ሲሆን÷በዛሬው እለትም ሽኝት ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡