አትሌት ታምራት ቶላ በኒውዮርክ ማራቶን ለአሸናፊነት ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ የማራቶን አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በመጪው ሕዳር በሚካሄደው ኒውዮርክ ማራቶን ለአሸናፊነት ይ በቃል፡፡
አትሌት ታምራት በ2023 በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
የፓሪስ ማራቶን አየር ንብረቱ እና የመንገዶቹ ሁኔታ ውድድሩን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር አስታውሶ ከዚህ ድካም በማገገም በኒውዮርክ ማራቶን አዲስ ክብረወሰን ለማስመዝገብ እንደሚሮጥ አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ከ1970 ጀምሮ አየተካሄደ የሚገኘው የኒውዮርክ ማራቶን ሕዳር 3 ቀን 2024 ላይ የሚካሄድ ሲሆን÷ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል ሲል ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
አትሌት ታምራት ውድድሩን በበላይነት ካጠናቀቀ በአንድ የውድድር ዓመት የኦሊምፒክ ማራቶን እና የኒውዮርክ ማራቶንን በማሸነፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኬንያዊቷ አትሌት ፕሬዝ ጂፕችርችር በመቀጠል ሁለተኛው ይሆናል፡፡