አየር መንገዱ በጎፋ ዞን ለተጎዱ ወገኖች ከ 6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የግንባታ ዕቃዎች ድጋፍ አድርጓል።
የአየር መንገዱ ፋውንዴሽን ክፍል ኃላፊ ሰናይት ንጉሴ ድጋፉን ለጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ(ኢ/ር) አስረክበዋል፡፡
አየር መንገዱ የመጀመሪያ ዙር 6 ሺህ ባለ 32 ኬጅ ቆርቆሮ እና 400 ኪሎግራም የቆርቆሮ ሚስማር በድምሩ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉንም ወይዘሮ ሰናይት ተናግረዋል።
ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር)፥በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ገልፀው አየር መንገዱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነነው መረጃ ያመላክታል ፡፡